+251463818559 info@amtvet.edu.et

የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክና የሳታላይት ኢንስቲትዩት የ100 ቀናት ዕድዱ አካል የሁኑ የተለያዩ ምርቶችን በማምረት ለገበያ አቀረበ፡፡

(አርባ ምንጭ፣ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም)

የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክና የሳታላይት ኢንስቲትዩት ተቋማዊ የገቢ ምንጮችአማራጭ ለማስፋ የሚያስችለው የ100 ቀናት ዕቅድን አዘጋጅቶ በሥራ ላይ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ም/ዲንና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዋና የሥራ ሂደት አተባባሪ የሆኑት አቶ ወርቅነህ ኃ/ሚካኤል ገለጹ፡፡  እንደ ም/ዲኑ ገለፃ ተቋሙ የዕቅዱ አካል ካደረጋቸው መካከል ለገጠር ግብርና ተኮር አገልግሎት የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን የማምረት ሥራ ይገኘበታል፡፡

በዚህም መሠረት በተቋሙ ብዛታቸው 20 ዘመናዊ የጀርመን የንብ ቀፎዎች እና እያንዳንዳቸው በአማካይ ከ35-40 ዶሮዎችን መያዝ የሚችሉ 8 ባለ ሁለት ደረጃ ዘመናዊ የዶሮ ቤቶች ተጠናቀው ለሽያጭ ተዘጋጅተዋል፡፡ እነዚህም ምርቶች የጥራት ደረጃውን በጠበቀ ጥሬ ዕቃዎች የተሠሩ ከመሆናቸውም በላይ የመሸጫ ዋጋቸውም ተመጣጣኝ በመሆናቸው ማንውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በመግዛት መጠቀም የሚችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ተቋሙ የራሱን የገቢ ማስገኛ ምርቶችን የሚያመርት ኢንተርፕራይዝ ያቋቋመ በመሆኑ በማንኛውም ሰዕት በግልም ሆነ በመ/ቤት ደረጃ በትዕዛዛትም ሆነ በጨረታ ተቀብሎ የሸክላ ጡብ፣ የተለያዩ ዲዛይን ያላቸው ቴራዞ፣ የእንስሳት መኖ መከትከቻ ማሽን፤ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽን /ፒሌት/፣ ባለ 4 ተንቀሳቃሽ በሎኬት ማምረቻ ማሽን እና ሌሎችን የቤትና የቤት ዕቃዎችችን ለመሥራት የሚያስችለው በመሆኑ፤ ተጠቃሚዎች በተያዘላችሁ ቀጠሮ በጥራት አምርቶ የሚያስረክ በመሆኑ የአርባ ምንጭ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች በዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

(የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት)