+251463818559 info@amtvet.edu.et

የአርባምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳታላይት ኢንስቲትዩትን በ ISO (International Organization for Standardization) ደረጃ ለማሳደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ዙሪያ ለአጠቃላይ አሠልጣኞችና አስተዳደር ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አደረገ፣

አርባ ምንጭ ግንቦት 11/2018 ዓ.ም.፣

የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳታላይት ኢንስቲትዩት የተቋሙን ደረጃ ወደ የISO21001 ስታንዳርድ ለማሳደግ የሚረዳውን ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ እንደሚግኝ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ በዛብህ ባርዛ ገለፁ፡፡

አቶ በዛብህ ባርዛ በገለፃቸውም የተቋሙን ደረጃ ወደ የISO21001 ስታንዳርድ ከፍታ ማሳደጉ አለማቀፋዊ ተወዳዳሪ የሆነ ሥልጠና የሚሰጥ ተቋም በመፍጠር ምሩቃኑን ጨምሮ በኮሌጁ የሚሰጠው ማንኛውም ምርትና አገልግሎት በማንኛውም ዓለም ተወዳዳሪና ተመራጭ ለማድረግ ሚረዳው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዚህም መሠረት ለዚሁ ተግባር የሚረዳ በአቶ ሞላልኝ በቀለ (ም/ዲን) የሚመራ ሰነድ ዝግጅት የሚያደርግ ግብረ-ሀይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ የገባ ሲሆን፤ አጠቃላይ የኮሌጁ ማህበረሰብም ለዚህ ኮሌጁን በአለማቀፋዊ ደረጃ ተወዳዳሪ ሊያደርግ ለሚያስችለው ISO-21001 ተግባራዊ እንቅስቃሴ በተሰማሩበት ሙያ እና የሥራ መስክ ተጨባጭ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ጥሪ አድርገዋል፡፡ ለዚህ ዕቅድ መሳካት ኮሌጁ ባለው አቅም ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንና ምንም እንኳን ወቅቱ ከፍተኛ የሀብት እጥረት ያለበት ቢሆንም ቁጠባን መሠረት ያደረገ ትግበራን መከተል እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም ማንኛውም የኮሉጁ ማህበረሰብ በተፈለገበት ቦታ ሁሉ በመገኘት የሚፈለግበትን የሙያዊም ይሁን የጉልበት አስተዋፅዎ የማበርከት ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ተገንዝቦ አስፈላጊውነት ትብብር እንዲደርግ አሳስበው፤ ይሁን እንጂ ከዚህ ዓላማ ውጭ ተግባሩን የሚጎትት ወይም የሚያደናቅፍ እንቅስቃሴ የማፈቀድና ኮሌጁም የማይታገስ መሆኑን በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡

የአርባምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ህዝብ ግንኙነት