(አርባምንጭ፣ ሚያዚያ 20/2018 ዓ.ም)
በአርባምንጭ ፖሊቴክኒክና የሳታላይት ኢንስቲትዩት ለዓመታት ተመስርቶ ተቋቁሙን እና አሠልጣኝ መምህራንን በማገናኘትና ድልድይ በመሆን ሲያገለግል ቆይቶ የነበረው መሠረታዊ የመምህራን ማህበር በተቋሙ ሥራ እንዳይሠራ ታግዶ መቆየቱን የኮሌጁ ዲን አቶ በዘዛብህ ባርዛ ገለፁ፡፡ እንደ ዲኑ ገለፃ የዕገዳዉ ምክንያት የመሠረታዊ ምህራን ማህበሩ አመራር አባላት ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የተቋሙን አሠራር ሊያዉክ የሚችል ተግባራ ላይ በመሰማራታቸው አና ከዚህም አድራጎታቸው በተደጋጋሚ እንዲቆጠቡና በማህበራቸው ግገ ደንብ የተቀመጠላቸውን ተግባራት ብቻ ላይ አተኩረው እንዲንቀሳቀሱ የተሰጣቸውን ምክር ሊቀበሉ ባለመቻላቸው በመሆኑ ሲሆን፤ ይህንንም ጉዳይ በጽሁፍ ለሚመለከታቸው የበላይ መዋቅሮች በማሳወቅ መንግስታዊ የሥራ ተግባራት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ሲባል የማህበሩን እንቅስቃሴን አግደው የቆዩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በመሠረታዊ መምህራኑ መታገድ ምክንያት ተቋማዊ አሠራሩ የተሟላ እንደማያደርገው ከቦርድ አመራር በተሰጠው አቅጣጫ እና ከመምህራኑም አየተነሳ በመሆኑ በአዲስ ተዋቆሮ ወደ ሥራ በመግባት ማህበሩ ከተቋሙ ጋር በመሆን ለመምህራኑ መብትና ጥቅማ ጥቅም እንዲሁም ለሥልጠና ጥራት የሚያበረክተውን ተግባር ሊቀጥል ይገላል በማለት ያቀረቡትን ጥሪ መነሻ በማድረግ ኮሌጁ ይህንን ጥያቄ ለአርባ ምንጭ ሪጅዮ ፖሊስ እና ለደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በማቅረብ በዛሬው ዕለት የሚመለከታቸው የማህበሩ የክልልና የከተማ አስተዳደሩ አመራር በመገነት እና አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በመካከላቸው መገኘታቸውል ግልጸዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ ከአርባ ምንጭ ሪጅዮ ፖሊስ ከተማ መምህራን ማህበር ጽ/ቤት እና ከተቁሙ አመራር የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው የመጡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ መሠረታዊ ማህበሩ ከአባለት የሚሰበሰበውን መዋጮ በህገ-ደንቡ መሠረት ፈሰስ ባለማድረጉና ወቅታዊ የሥራ ሪፖር ባለማድረጉ ተቋርጦ መቆየቱን ገልጸው፤ ይሁንና አባላቱ የሚፈለግባቸውን ወርሃዊ መዋጮ እስከ ዛሬ እየከፈሉ የቆዩ በመሆናቸው፤ ነገር ግን የመሠረታዊ መምህራን ማህበሩ አመራር የመሪ ተመሪ መርህን ባለመከተል ምክንያ በፈጠሩት ክፍተት ተጎጂ መሆን ስለሌለባቸው ማህበሩን አዲስ ለማዋቀር የመጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የቀድሞ መሠረታዊ መምህራን ማህበሩ ሊቀመንበር የነበሩት ኢ/ር ፀጋዬ አፈወርቅ በተቋሙ ኃላፊዎች የመምህራንን ጥቅማ ጥቅም ከመፈፀም አንፃር እደረሰ በነበረው ጫና ከተቋማቸው ጋር መግባባት ባለመቻላቸው እገዳ እንደተጣለባቸው እና ጉዳዩንም ለሚመለከታቸው የበላይ አካላት ብናሳውቅም ተገቢ ምላሽ ለማግኘት ባለመቻላችን መተላለፍ የነበረበትን ፈሰስ የመምህራኑን መብት ለማስከበር በተንቀሳቀስንበት ሂደት ገንዘብ ስላልበቃቸው መጠቀማቸውን ገልፀው ይህም አግባብ ባይሆንም ምርጫ በማጣት ያደረጉት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በስብሰባው ላይ የደ/ኢ/መ/ማ እና የአ/ም/ሪ/ፖ/ መም/ማ/ ሥራ አስፈፃሚዎች ተግተዋል፡፡ የደ/ኢ/መ/ማ/ ዋና ፀኃፊ አቶ ጌታቸው ስለ ተሸሻለው መተዳደሪያ ህገ-ደንብ ገለፃ አድርገዋል፡፡ መጨረሻም በኢንስትራክተር አሸናፊ ዋሸራ ሊቀመንበርነት የሚመራ አምስት አዳዲስ የሥራ አስፈፃሚ አመራርን በማስመረጥ ማህበሩ በአዲስ ተዋቅሮ ተመራጮቹም ቃለ-መሃላ ገብተው ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል፡፡
(የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት)