የአርባምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በሶዶ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ልምድ የልውውጥ አደረገ፣
አርባ ምንጭ ግንቦት 04/2018 ዓ.ም.፣
የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳታላይት ኢንስቲትዩት የተቋሙን ደረጃ ወደ የISO21001 ለማሳደግ የሚረዳውን የልምድ ልውውጥ ቀድሞ የሰነድ ዝግጅት በማጠናቀቅ ወደ ትግበራ ከገባው የሶዶ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ለወውውጥ አደረገ። የሶዶ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ኢ/ር ያዕቆብ ያሲን አሁን የደረሱበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ ዉጣ ውረዶችን ያለፉ መሆኑን ጠቅሰዉ ይሁንና ቁርጠኛ አመለካከት ያላቸውን አስፈፃሚ ኮሚቴዎችንና አመራር በመያዙ መሆኑን በመግለጫቸው በዝርዝር አስረድተው ወደ ተቋማቸው ለልምድ ልውውጥ በመምጣታችሁ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል። በተጨማሪም የታስክ ፎርሱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ እምሩ በሰነድ ዝግጅት ሂደት ወቅት ስለሄዱባቸው መንገዶች በዝርዝር አስረድተው የባለሙያዎቹ ቡድን ለኮሌጃችን ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ዲን አቶ በዛብህ ባርዛ ኮሌጁ በቀናነት ላካፈላቸው ልምድ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው ባገኙት ልምድ ተጠቅመው በቅርቡ የሰነድ ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ገልጸዋል።
የአርባምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ህዝብ ግንኙነት