አርባ ምንጭ፣ ሚያዚያ 14/2018 ዓ.ም.
ADRA Ethiopia – Adventist Development and Relief Agency (Ethiopia) መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ ደርጅቱ ከዚህ በፊት በ Green TVET ፕሮግራም ላይ ከአርባ ምንጭ መካነ የሱስ ኮሌጅ ጋር በመሥራት የሚታወቅ ውጤታማ ድርጅት ሲሆን የነበረውን የሥራ ጊዜውን አጠናቆ በአሁኑ በ Phase III ፕሮግራሙ ከኮሌጃችን ጋር Green TVET and Digitalization ለመሥራት ያለውን ፍላጎት እውን ማድረግ የሚያስችለውን በድርጅቱ ፕሮጀክት ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዳዊት መሃሪ የተመራ ልዑካን ቡድን በአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በመገኘት ተቋማዊ ምልከታ እና ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይታቸውም ላይ ትኩረት ሰጥተው ማብራሪያ የጠየቁበት ኮሌጁ በተለይም ዲጅታላይዜሽንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለው የመሠረተ-ልማት ዝግጁነት ምን እንደሚመስል ነበር፡፡
የኮሌጁ ዲን አቶ በዛብህ ባርዛ በቅድሚያ ADRA Ethiopia ኮሌጃችንን መርጦ ከእኛ ጋር ለመሥራት ፈቃደኛ ሆኖ ስለመጣ ታላቅ ምስጋና አቅርበው ኮሌጁ ዲጅታላይዜሽንን ተግባራዊ ለማድረግ ሰፊ የመሠረተ-ልማት ዝግጁነት ያለው መሆኑን አብራርተው ድርጅቱ ወደ ተቋማችን ሲመጣ በተመቻቸ ሁኔታ ላይ ሥራ እንደሚጀምር ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዚህም ፕሮግራም ላይ የድርጅቱ ክፍተኛ አመራሮች ዶ/ር ጌታቸው፣ ዶ/ር ኦርካይዶ፣ አቶ አስመላሽና ሌሎች የልዑካን ቡድን አባላት እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን በኮሌጁ በኩልም ም/ዲኑ አቶ ሞላልኝ በቀለን ጨምሮ የኮሌጁ ማህበረሰብ ተገኝተዋል፡፡
በመጨረሻም ለልዑካን ቡድኑ የማስታወሻ ስጦታ በኮሌጁ ተበርክቶላቸዋል፡፡
(የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት)