+251463818559 info@amtvet.edu.et

​የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ(ዶ/ር) የተመራ የልዑካን ቡድን በአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ እና በሳተላይት ማዕከላት የሚከናወኑ የተለያዩ ሥራዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።በምልከታው ወቅት አበባየሁ(ዶ/ር) የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ለሀገር ዕድገት የጀርባ አጥንት በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። በክትትልና ቁጥጥር ወቅት የታዩ ውጤቶች አበረታች መሆናቸውን የገለጹት ኃላፊው በቀጣይም ከዚህ በተሻለ መልኩ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።​የጋሞ ዞን የሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሐኪሜ አየለ በበኩላቸው በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ውጤታማና በክህሎት የበቁ ወጣቶችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።በኮሌጁ እየተከናወኑ ያሉ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች ለወጣቱ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ፣ ለሀገር ዕድገት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማሟላት ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ መሆኑንም ጠቁመዋል።​​የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲን አቶ በዛብህ ባርዛ መንግስት እያደረገ ያለው ድጋፍ ለሥራው መሳካት ትልቅ አቅም መሆኑን ገልጸው ኮሌጁ በምርምርና በፈጠራ ዘርፍ ውጤታማ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።በተለይም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በማጠናከር ረገድ ሰፊ ሥራዎች እየተሰሩ በመሆኑን ​ወጣቶች በክህሎት ስልጠና ተገቢውን ዕውቀት አግኝተው ወደ ኢንዱስትሪው እንዲቀላቀሉ እየተደረገ ነው ብለዋል።​ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ አዳዲስ ማሽነሪዎችን በማምረት ረገድም ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን አብራርተዋል።​ሠልጣኝ ተማሪዎችም የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ሥልጠና እንዲያገኙና በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥራ ባህል እንዲያዳብሩ ተቋሙ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።​በጉብኝቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ፣ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሐኪሜ አየለን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።