የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ሥልጠና ከጀመረበት ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ ወቅታዊ የአካባቢያዊና ሀገራዊ የሰው ኃይል ገበያ ፍላጎት መሠረት አድርገው በሚቀያየሩ የሙያ ዓይነቶችና ደረጃዎች ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ባለሙያዎችን ሲያፈራ የቆየ አንጋፋና ፈር ቀዳጅ ተቋም ነው፡፡ኢንስቲትዩቱ ማሠልጠን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለዞናችን፣ ለአጎራባች ዞኖች፣ ለክልሉና ብሎም ለመላው ሀገሪቷ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉ በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠኑ የዛሬዎቹን ጨምሮ በ27 ዙር 21,157 ባለሙያዎችን አፍርቷል፡፡ በ 01/02/2018 ኮሌጁ 376 ሠልጣኞችን በተለያዩ ሙያዎች እና ደረጃዎች አሰልጥኖ ብቁ በማድረግ ያስመርቃል፡፡ የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በዲግሪ ፕሮግራምም ለ6ኛ ዙር በአጠቃላይ እነዚህን ጨምሮ 258 ተመራቂዎችን አፍርቷል፡፡ ይህም አጠቃላይ የተቋማችንን የምሩቃ ቁጥር ወደ 21,415 ያደርሰዋል ማለት ነው፡፡የ27 ዙር ምሩቃን እንኳን ደስ አላችሁ!!!!!!!
CONGRATULATIONS!!!!!