አርባ ምንጭ፣ ጥቅምት 01፣ 2018 (ዓ.ም) – የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በተለያዩ የቴክኖሎጂ ሙያዎች 376 ሠልጣኞችን አሰልጥኖ በማስመረቅ የትምህርት ዘመኑን አጠናቋል።

በማስመረቂያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሰልጣኝ አሰልጣኝ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዳዊት ፋንታዬ እንዳሉት ፣ እነዚህ ተማሪዎች በሀገራችን ኢንዱስትሪ እና ኢኮኖሚ ልማት ውስጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ አሳስበዋል። “ዛሬ የምናስመርቀው ወጣቶች በሀገራችን የሚካሄደው የልማት ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ክፍሎች ናቸው” ብለዋል።

የተመረቁት ተማሪዎች በተለያዩ ዲፕሎማ ፕሮግራሞች ሲሆኑ፣ በመካከላቸውም የኢሌክትሪክሲቲ፣ ጋርመንት ቴክኖሎጂ፣ ሆቴል ማኔጅመንት ፣ የሰርቬይንግ ኢንጅነሪንግ እና አይሲቲ ወዘተ የተለያዩ ሙያዎች ይገኙበታል።

በተማሪዎቹ መካከል የናገርናችሀው አንዳንድ ተማሪዎች እንደተናገሩት፣ “በኢንስቲትዩቱ የተሰጠን ትምህርት እና ሙያዊ ስልጠና በሙያችን ብቁ እንድንሆን አስቻሎናል። አሁን ወደ ሥራ ዓለም ለመግባት ዝግጁ ነን” ብለዋል።

የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በሀገሪቱ ከሚገኙት የቴክኒክእና ሙያ ትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን በተለይም የቴክኖሎጂ ትምህርት እና ምርምር ይታወቃል። ተቋሙ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚክ ልማት አስፈላጊ የሆኑ የቴክኒክ እና ሙያ እውቀት ያላቸው ዜጎችን በማፍራት ይታወቃል።