+251463818559 info@amtvet.edu.et

የአርባምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳተላይት ኢንስቲትዩት ለተማሪዎች ለመምህራን እና ለሌሎች አሰተባባሪ ባለድርሻ አካላት በ2018 ዓ.ም. አዲስ ገቢ ተማሪዎች ላይ የሚካሄደውን የሳይኮሜትሪክ ፈተና (Psychometric TVET Placement System) በሚመለከት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ።

በተለይም የአካዳሚክ ጉዳዮች  ዋና ሃላፊ የሆኑት አቶ ሞላለኝ በቀለ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ እንዳሉት በዚህ ወቅት የሳይኮሜትሪክ ፈተናው ተማሪዎች በራሳቸው ፍላጎት፣ ችሎታ እና ዝንባሌ በሚስማማቸው የሙያ መስክ እንዲመዘገቡ የሚያረጋግጥ ቁልፍ አካል እንደሆነ አመልክተዋል።

አቶ ሞላለኝ በተጨማሪም በ2018 ዓ.ም. ለሚገቡ ሁሉም ተማሪዎች የስራና ክህሎት ሚኒስቴር (Ministry of Labor and Skills) መመሪያ መሰረት ይህን የሳይኮሜትሪክ ፈተና ከማለፋቸው በፊት የሚመረጡትን የትምህርት መስክ መጀመር እንደማይችሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።