በኢፌድሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች በአርባምንጭ ከተማና በጋሞ ዞን በዘርፉ የተከናወኑ ስራዎችን በሥፍራው ተገኝተው እየተመለከቱ ይገኛሉ።
ልዑካን ቡድኑ በአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ጉብኝት ያደረገ ሲሆን፣ በቆይታቸውም የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች፤የተደራጁ ማህበራት እንቅስቃሴና የካይዘን አተገባበር፤የጋርመንት ስራዎች እና የጄኔራል ፋብሪኬትድ ሜታል ወርክሾፕ ተግባራት፤ የባዮ ሜዲካል ክፎሎችና አተገባበር እንዲሁም አጠቃላይ የሥራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች ተጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የማህበራት አደረጃጀትና የስራ ዕድል ፈጠራ፤ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ የስራ ስምሪቶች፤ ሀገራዊ ኢኒሼቲቮችን የመተግበር ሂደት ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።
አጫጭር ስልጠናዎች እና የሥራ ስምሪቱ ጋር በተያያዘ የተከናወኑ ተግባራትና ክህሎት መር የስራ ስምሪት ከሚሰራው ስራ አስቀድሞ ስለስራው ግንዛቤ የመፍጠር እንደመሆኑ በዘርፉ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም በምልከታው የኢፌድሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ አንስተዋል።
የስልጠና ጥራት ተደራሽነት እና የገቢ ማመንጫ ስራዎች ላይም ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባም አንስተዋል።
ተቋሙ ያልተገቡ ስልጠናዎችን በመዝጋት ተፈላጊና ለወጣቱ የስራ ዕድል በሚፈጥሩ የስራ ስምሪቶች ላይ ማተኮሩ አበረታች መሆናቸውም ተነስቷል ።
የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ዲን አቶ በዛብህ ዳርዛ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትና መልካም አጋጣሚዎችን እና ተግዳሮቶችን ለቡዱኑ አቅርበዋል ።
የሙያ ምልከታዎችና ውይይቶች ለዘርፉ እድገትና ለወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።
ጉብኝቱ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚታዩ ጠንካራ ጎኖችን ለማጠናከርና ክፍተቶችን በጋራ ለመፍታት ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።
ጥር 1/2018 ዓ.ም፤